17 በመሆኑም ኢያሱ ለዮሴፍ ቤት ይኸውም ለኤፍሬምና ለምናሴ እንዲህ አለ፦ “እናንተ ብዙ ሕዝብ ናችሁ፤ ታላቅ ኃይልም አላችሁ። ድርሻችሁ አንድ ዕጣ ብቻ አይሆንም፤+ 18 ከዚህ ይልቅ ተራራማው አካባቢ የእናንተ ይሆናል።+ አካባቢው ጫካ ቢሆንም ትመነጥሩታላችሁ፤ የግዛታችሁም ወሰን ይሆናል። ምክንያቱም ከነአናውያን የብረት ማጭድ የተገጠመላቸው የጦር ሠረገሎች ያሏቸውና ብርቱዎች ቢሆኑም እንኳ ከምድሩ ታባርሯቸዋላችሁ።”+