27 ወገቡ ከሚመስለው ነገር ጀምሮ ወደ ላይ፣ እሳት የሚመስል እንደ ብረት የሚያብረቀርቅ ነገር+ ሲወጣ አየሁ፤ ደግሞም ከወገቡ ጀምሮ ወደ ታች፣ እሳት የሚመስል ነገር አየሁ።+ በዙሪያውም ደማቅ ብርሃን ነበር፤ 28 ይህም ዝናባማ በሆነ ቀን በደመና ውስጥ እንደሚታይ ቀስተ ደመና ነበር።+ በዙሪያው ያለው ደማቅ ብርሃን ይህን ይመስላል። ደግሞም የይሖዋን ክብር ይመስል ነበር።+ እኔም ባየሁት ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ፤ ከዚያም አንዱ ሲናገር ድምፅ ሰማሁ።