ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘሌዋውያን 10–11
ለይሖዋ ያለን ፍቅር ለቤተሰባችን ካለን ፍቅር ሊበልጥ ይገባል
አንድ የቤተሰባችን አባል ሲወገድ ለይሖዋ ያለን ታማኝነት በእጅጉ ሊፈተን ይችላል። ይሖዋ ለአሮን የሰጠው መመሪያ፣ ከተወገደ የቤተሰባቸው አባል ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማቋረጥ ለሚያስፈልጋቸው ክርስቲያኖች ግልጽ መልእክት ይዟል። ለይሖዋ ያለን ፍቅር፣ ታማኝ ላልሆኑ የቤተሰባችን አባላት ካለን ፍቅር መብለጥ ይኖርበታል።
ይሖዋ ከተወገደ ሰው ጋር በተያያዘ የሰጠውን መመሪያ የሚከተሉ ሰዎች ምን በረከቶች ያገኛሉ?—1ቆሮ 5:11፤ 2ዮሐ 10, 11