የግርጌ ማስታወሻ
አንዳንድ ባለሙያዎች እንደሚመክሩት አብዛኛውን ጊዜ፣ ከባድ የምግብ አለርጂ ያለባቸው ሰዎች ድንገት ችግሩ ቢያጋጥማቸው ራሳቸውን መርፌ መውጋት እንዲችሉ የአድሬናሊን (ኤፒኔፍሪን) መርፌ መያዛቸው ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። አለርጂ ያለባቸው ልጆች አስተማሪዎቻቸው ወይም እንክብካቤ የሚሰጧቸው ሰዎች ስለ ችግራቸው እንዲያውቁ ለማድረግ አለርጂ ስለሚሆኑባቸው ነገሮች የሚናገር ሰነድ እንዲይዙ ወይም እንዲያስሩ አንዳንድ የጤና ባለሙያዎች ይመክራሉ።