የግርጌ ማስታወሻ
b በዳንኤል 2:44 ላይ የሚገኘው “እነዚያን መንግሥታት ሁሉ ያደቃል” የሚለው ሐረግ የሚያመለክተው በምስሉ የተለያዩ ክፍሎች የተመሰሉትን መንግሥታት ወይም የዓለም ኃያላን ነው። ይሁንና ስለ ተመሳሳይ ጉዳይ የሚናገር ሌላ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት፣ ‘በታላቁ የአምላክ ቀን’ ላይ ‘የዓለም ነገሥታት ሁሉ’ በይሖዋ ላይ እንደሚነሱ ይገልጻል። (ራእይ 16:14፤ 19:19-21) በመሆኑም በአርማጌዶን የሚጠፉት በምስሉ ላይ የተገለጹት መንግሥታት ብቻ ሳይሆኑ ሁሉም ሰብዓዊ መንግሥታት ናቸው።