ዘፍጥረት 35:18, 19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 እሷ ግን ሕይወቷ ሊያልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች* (ሞት አፋፍ ላይ ስለነበረች) የልጁን ስም ቤንኦኒ* አለችው፤ አባቱ ግን ስሙን ቢንያም*+ አለው። 19 ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ይኸውም ወደ ቤተልሔም+ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች። ዘፍጥረት 42:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው።+ ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።” ዘፍጥረት 44:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ ስንል መለስንለት፦ ‘አረጋዊ አባት አለን፤ እንዲሁም በስተርጅናው የወለደው የሁላችንም ታናሽ የሆነ ወንድም አለን።+ ወንድሙ ግን ሞቷል፤+ በመሆኑም ከአንድ እናት ከተወለዱት መካከል የቀረው እሱ ብቻ ነው፤+ አባቱም በጣም ይወደዋል።’
18 እሷ ግን ሕይወቷ ሊያልፍ በማጣጣር ላይ ሳለች* (ሞት አፋፍ ላይ ስለነበረች) የልጁን ስም ቤንኦኒ* አለችው፤ አባቱ ግን ስሙን ቢንያም*+ አለው። 19 ራሔልም ሞተች፤ ወደ ኤፍራታ ይኸውም ወደ ቤተልሔም+ በሚወስደው መንገድ ላይ ተቀበረች።
38 እሱ ግን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ከእናንተ ጋር ወደዚያ አይወርድም። ምክንያቱም ወንድሙ ሞቷል፤ አሁን የቀረው እሱ ብቻ ነው።+ ከእናንተ ጋር አብሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አደጋ ቢደርስበትና ቢሞት ሽበቴን በሐዘን+ ወደ መቃብር*+ ታወርዱታላችሁ።”
20 እኛም ለጌታዬ እንዲህ ስንል መለስንለት፦ ‘አረጋዊ አባት አለን፤ እንዲሁም በስተርጅናው የወለደው የሁላችንም ታናሽ የሆነ ወንድም አለን።+ ወንድሙ ግን ሞቷል፤+ በመሆኑም ከአንድ እናት ከተወለዱት መካከል የቀረው እሱ ብቻ ነው፤+ አባቱም በጣም ይወደዋል።’