7 በእርሻ መካከል ነዶ እያሰርን ነበር፤ ከዚያም የእኔ ነዶ ተነስታ ቀጥ ብላ ስትቆም የእናንተ ነዶዎች ደግሞ የእኔን ነዶ ከበው ሰገዱላት።”+ 8 ወንድሞቹም “በእኛ ላይ ንጉሥ ልትሆንና ልትገዛን ታስባለህ ማለት ነው?” አሉት።+ በመሆኑም ያየው ሕልምና የተናገረው ነገር እሱን ይበልጥ እንዲጠሉት አደረጋቸው።
9 ከዚያም ሌላ ሕልም አለመ፤ ሕልሙንም ለወንድሞቹ እንዲህ ሲል ነገራቸው፦ “ሌላም ሕልም አለምኩ። አሁን ደግሞ ፀሐይ፣ ጨረቃና 11 ከዋክብት ሲሰግዱልኝ አየሁ።”+