23 “አንተም ጥሩ መዓዛ ያላቸውን የሚከተሉትን ምርጥ ቅመሞች ውሰድ፦ 500 ሰቅል የረጋ ከርቤ፣ የዚህን ግማሽ ይኸውም 250 ሰቅል ጣፋጭ ቀረፋ፣ 250 ሰቅል ጥሩ መዓዛ ያለው ጠጅ ሣር፣ 24 እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል መሠረት+ 500 ሰቅል ብርጉድ እንዲሁም አንድ ሂን የወይራ ዘይት። 25 ከእነዚህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት አዘጋጅ፤ በብልሃት የተቀመመ መሆን ይኖርበታል።+ ይህም ቅዱስ የቅብዓት ዘይት ይሆናል።