-
ዘሌዋውያን 8:18-21አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እሱም ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን አውራ በግ አመጣ፤ አሮንና ወንዶች ልጆቹም እጆቻቸውን በአውራው በግ ራስ ላይ ጫኑ።+ 19 ከዚያም ሙሴ አውራውን በግ አረደው፤ ደሙንም በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው። 20 አውራውንም በግ በየብልቱ ቆራረጠው፤ ቀጥሎም ጭንቅላቱን፣ ብልቶቹንና ሞራውን* አጨሰው። 21 ሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠባቸው፤ ሙሴም አውራው በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ አደረገ። ይህም ደስ የሚያሰኝ* መዓዛ ያለው የሚቃጠል መባ ነበር። ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ነበር።
-
-
ዘሌዋውያን 9:12-14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
12 ከዚያም የሚቃጠል መባ ሆኖ የሚቀርበውን እንስሳ አረደው፤ ወንዶች ልጆቹም ደሙን ሰጡት፤ እሱም ደሙን በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ረጨው።+ 13 እነሱም የሚቃጠለውን መባ ብልቶች ከነጭንቅላቱ ሰጡት፤ እሱም በመሠዊያው ላይ እንዲጨሱ አደረገ። 14 በተጨማሪም ሆድ ዕቃውንና እግሮቹን አጠባቸው፤ በመሠዊያው ላይ ባለው በሚቃጠለው መባ ላይም እንዲጨሱ አደረገ።
-