ማቴዎስ 5:43, 44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 “‘ባልንጀራህን ውደድ፤+ ጠላትህን ጥላ’ እንደተባለ ሰምታችኋል። 44 እኔ ግን እላችኋለሁ፦ ጠላቶቻችሁን ውደዱ+ እንዲሁም ስደት ለሚያደርሱባችሁ ጸልዩ፤+ ማቴዎስ 22:39 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 39 ሁለተኛውም ይህንኑ የሚመስል ሲሆን ‘ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ’ ይላል።+ ሮም 13:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል። ገላትያ 5:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 መላው ሕግ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ” በሚለው አንድ ትእዛዝ ተፈጽሟልና።*+ ያዕቆብ 2:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 እንግዲያው በቅዱስ መጽሐፉ መሠረት “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ የሚለውን ንጉሣዊ ሕግ ተግባራዊ የምታደርጉ ከሆነ መልካም እያደረጋችሁ ነው።
9 ምክንያቱም “አታመንዝር፣+ አትግደል፣+ አትስረቅ፣+ አትጎምጅ”+ የሚሉት ሕጎችና ሌሎች ትእዛዛት በሙሉ “ባልንጀራህን* እንደ ራስህ ውደድ”+ በሚለው በዚህ ቃል ተጠቃለዋል።