ዘፍጥረት 9:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 አምላክ ሰውን በአምሳሉ ስለሠራው+ የሰውን ደም የሚያፈስ ማንም ሰው የእሱም ደም በሰው እጅ ይፈስሳል።+ ዘፀአት 21:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “አንድ ሰው ሌላውን ሰው መትቶ ቢገድል ገዳዩ ይገደል።+ ዘኁልቁ 35:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ሞት ለሚገባው ነፍሰ ገዳይ ሕይወት* ቤዛ አትቀበሉ፤ ምክንያቱም ያለምንም ጥርጥር መገደል አለበት።+ ዘዳግም 19:11-13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+ 13 አትዘንለት፤* መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ።+
11 “ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፣+ አድብቶም ለሞት የሚያበቃ ጉዳት ቢያደርስበትና ሰውየው ቢሞት፣ ገዳዩም ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዱ ቢሸሽ 12 የሚኖርበት ከተማ ሽማግሌዎች ሰውየውን ከዚያ በማስመጣት ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት፤ ይህ ሰው ሞት ይገባዋል።+ 13 አትዘንለት፤* መልካም እንዲሆንልህ ንጹሕ ደም በማፍሰስ የሚመጣን በደል ከእስራኤል አስወግድ።+