ዘፍጥረት 12:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ይሖዋም ለአብራም ተገለጠለትና “ይህችን ምድር ለዘርህ+ እሰጣለሁ”+ አለው። ስለዚህ አብራም ተገልጦለት ለነበረው ለይሖዋ በዚያ መሠዊያ ሠራ። ዘዳግም 4:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ መሐሪ አምላክ ነው።+ አይተውህም፣ አያጠፋህም ወይም ለአባቶችህ በመሐላ ያጸናላቸውን ቃል ኪዳን አይረሳም።+ መዝሙር 106:45 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 45 ለእነሱ ሲል ቃል ኪዳኑን ያስታውስ ነበር፤ታላቅ በሆነው* ታማኝ ፍቅሩ ተገፋፍቶ ያዝንላቸው* ነበር።+