ዘፍጥረት 30:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ራሔልም “ከእህቴ ጋር ብርቱ ትግል ገጠምኩ፤ አሸናፊም ሆንኩ!” አለች። በመሆኑም ስሙን ንፍታሌም*+ አለችው። ዘፍጥረት 35:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ከራሔል አገልጋይ ከባላ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዳንና ንፍታሌም ነበሩ። ዘፍጥረት 46:24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 24 የንፍታሌም+ ወንዶች ልጆች ያህጽኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሺሌም ነበሩ።+ 1 ዜና መዋዕል 7:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 የንፍታሌም ወንዶች ልጆች+ ያህጺኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሻሉም ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች የባላ+ ዘሮች* ነበሩ።