15 “ከሰውም ሆነ ከእንስሳ ለይሖዋ የሚያቀርቡት የእያንዳንዱ ሕይወት ያለው ነገር በኩር ሁሉ+ የአንተ መሆን ይኖርበታል። ሆኖም ከሰው በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይኖርብሃል፤+ እንዲሁም ርኩስ ከሆነ እንስሳ በኩር የሆነውን ሁሉ መዋጀት ይገባሃል።+ 16 አንድ ወርና ከዚያ በላይ ሲሆነው እንደ ቋሚ መለኪያ ሆኖ በሚያገለግለው በቅዱሱ ስፍራ ሰቅል+ መሠረት በተተመነለት ዋጋ ይኸውም በአምስት የብር ሰቅል ወጆ ልትዋጀው ይገባል። አንዱ ሰቅል 20 ጌራ ነው።