-
ዘኁልቁ 3:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ሌዋውያኑን ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ ስጣቸው። እነሱ የተሰጡ ናቸው፤ ከእስራኤላውያን መካከል ለእሱ የተሰጡ ናቸው።+
-
-
1 ዜና መዋዕል 23:32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 በተጨማሪም በይሖዋ ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ከመገናኛ ድንኳኑ፣ ከቅዱሱ ስፍራና ወንድሞቻቸው ከሆኑት የአሮን ወንዶች ልጆች ጋር በተያያዘ ያሉባቸውን ኃላፊነቶች ይወጡ ነበር።
-
-
ሕዝቅኤል 44:11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
11 ከዚያም በመቅደሴ የቤተ መቅደሱን በሮች የሚቆጣጠሩ+ እንዲሁም በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚያገለግሉ አገልጋዮች ይሆናሉ። ሙሉ በሙሉ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕት ለሕዝቡ ያርዳሉ፤ ደግሞም ሕዝቡን ለማገልገል በፊታቸው ይቆማሉ።
-