-
ዘሌዋውያን 2:14አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
14 “‘መጀመሪያ የደረሰውን ፍሬ የእህል መባ አድርገህ ለይሖዋ የምታቀርብ ከሆነ የደረሰውን ሆኖም ገና እሸት የሆነውን በእሳት የተጠበሰና የተከካ እህል መጀመሪያ ላይ እንደደረሰው ፍሬህ የእህል መባ አድርገህ አቅርብ።+
-
-
ዘዳግም 26:1, 2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
26 “አምላክህ ይሖዋ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር ገብተህ ስትወርስና በዚያ መኖር ስትጀምር 2 አምላክህ ይሖዋ ከሚሰጥህ ምድር ከምትሰበስበው ይኸውም ምድሪቱ ከምታፈራው ፍሬ ሁሉ በኩር የሆነውን ወስደህ በቅርጫት ውስጥ በማድረግ አምላክህ ይሖዋ ለስሙ ማደሪያ እንዲሆን ወደሚመርጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።+
-