ዘፀአት 20:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+ ዘፀአት 35:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ ለይሖዋም ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል።+ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደላል።+ ዘዳግም 5:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው።+
9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+
2 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእናንተ የተቀደሰ ይሆናል፤ ለይሖዋም ሙሉ በሙሉ የሚታረፍበት ሰንበት ይሆናል።+ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራ ማንም ሰው ይገደላል።+
13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው።+