6 ይሖዋም በፊቱ እያለፈ እንዲህ ሲል አወጀ፦ “ይሖዋ፣ ይሖዋ፣ መሐሪና+ ሩኅሩኅ+ የሆነ አምላክ፣ ለቁጣ የዘገየ፣+ ታማኝ ፍቅሩና+ እውነቱ+ እጅግ ብዙ የሆነ፣ 7 ታማኝ ፍቅርን ለሺዎች የሚያሳይ፣+ ስህተትን፣ መተላለፍንና ኃጢአትን ይቅር የሚል፣+ ጥፋተኛውን ግን በምንም ዓይነት ሳይቀጣ የማያልፍ+ እንዲሁም አባቶች ለሠሩት ስህተት በልጆች፣ በልጅ ልጆች፣ በሦስተኛና በአራተኛ ትውልድ ላይ ቅጣትን የሚያመጣ።”+