47 እነሱም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ባለው ክልል የነበሩትን የሁለቱን የአሞራውያን ነገሥታት ምድር ማለትም የሲሖንን ምድርና የባሳንን ንጉሥ የኦግን+ ምድር ወረሱ፤ 48 ይህም ምድር በአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ከሚገኘው ከአሮዔር+ አንስቶ እስከ ሲዎን ተራራ ይኸውም እስከ ሄርሞን+ ድረስ ያለውን አካባቢ ይሸፍናል፤ 49 እንዲሁም ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ የሚገኘውን የአረባን ምድርና በጲስጋ+ ሸንተረር ግርጌ እስከሚገኘው እስከ አረባ ባሕር ድረስ ያለውን አካባቢ ይጨምራል።