-
ኢያሱ 13:1-3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
13 ኢያሱም ዕድሜው ገፍቶና አርጅቶ ነበር።+ በመሆኑም ይሖዋ እንዲህ አለው፦ “እንግዲህ አንተ ዕድሜህ ገፍቷል፤ አርጅተሃል፤ ሆኖም መወረስ* ያለበት ገና ሰፊ ምድር ይቀራል። 2 የሚቀረውም ምድር ይህ ነው፦+ የፍልስጤማውያንና የገሹራውያን+ ምድር በሙሉ 3 (ከግብፅ ፊት ለፊት ከሚገኘው ከአባይ ወንዝ ቅርንጫፍ* አንስቶ በሰሜን እስከ ኤቅሮን ወሰን ድረስ ያለው ክልል የከነአናውያን ግዛት እንደሆነ ተደርጎ ይቆጠር ነበር)+ እንዲሁም በጋዛ፣ በአሽዶድ፣+ በአስቀሎን፣+ በጌት+ እና በኤቅሮን+ የሚኖሩትን የአምስቱን የፍልስጤም ገዢዎች+ ምድር የሚጨምር ሲሆን የአዊም+ ሰዎችንም ምድር ያካትታል፤
-
-
ኢያሱ 15:20አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 የይሁዳ ነገድ በየቤተሰባቸው የተሰጣቸው ርስት ይህ ነበር።
-
-
ኢያሱ 15:45አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
45 ኤቅሮን እንዲሁም በሥሯ* ያሉት ከተሞችና መንደሮቿ።
-