-
ዘፍጥረት 28:3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ይባርክሃል፤ ፍሬያማም ያደርግሃል፤ እንዲሁም ያበዛሃል፤ አንተም በእርግጥ ብዙ ሕዝብ ያቀፈ ጉባኤ ትሆናለህ።+
-
-
ዘፍጥረት 35:23-26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 ከሊያ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ የበኩር ልጁ ሮቤል+ ከዚያም ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ይሳኮር እና ዛብሎን ነበሩ። 24 ከራሔል የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዮሴፍና ቢንያም ነበሩ። 25 ከራሔል አገልጋይ ከባላ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ዳንና ንፍታሌም ነበሩ። 26 ከሊያ አገልጋይ ከዚልጳ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ደግሞ ጋድና አሴር ነበሩ። እነዚህ ያዕቆብ በጳዳንአራም ሳለ የወለዳቸው ወንዶች ልጆቹ ናቸው።
-
-
ዘፍጥረት 46:22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
22 እነዚህ ራሔል ለያዕቆብ የወለደችለት ወንዶች ልጆች ናቸው፤ እነሱም በአጠቃላይ 14* ነበሩ።
-
-
ዘፍጥረት 46:25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ላባ ለልጁ ለራሔል የሰጣት ባላ የተባለችው አገልጋይ የወለደቻቸው ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው። እሷም ለያዕቆብ እነዚህን ወለደችለት፤ እነሱም በአጠቃላይ ሰባት* ነበሩ።
-