1 ሳሙኤል 14:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 በመሆኑም ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን “ና፣ ወደ እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች የጦር ሰፈር እንሻገር።+ ይሖዋ በብዙም ሆነ በጥቂት ሰዎች ተጠቅሞ ከማዳን የሚያግደው ነገር ስለሌለ ምናልባት ይሖዋ ስለ እኛ ሲል እርምጃ ይወስድ ይሆናል” አለው።+ 2 ሳሙኤል 5:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ዳዊትም ይሖዋን ጠየቀ፤ እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዞረህ በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት ለፊት ግጠማቸው። 24 በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ቆራጥ እርምጃ ውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ ይሖዋ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።” 2 ነገሥት 6:15, 16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሲወጣ በፈረሶችና በጦር ሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ከተማዋን መክበቡን አየ። አገልጋዩም ወዲያውኑ “ወየው ጌታዬ! ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ። 16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው።
6 በመሆኑም ዮናታን ጋሻ ጃግሬውን “ና፣ ወደ እነዚህ ያልተገረዙ ሰዎች የጦር ሰፈር እንሻገር።+ ይሖዋ በብዙም ሆነ በጥቂት ሰዎች ተጠቅሞ ከማዳን የሚያግደው ነገር ስለሌለ ምናልባት ይሖዋ ስለ እኛ ሲል እርምጃ ይወስድ ይሆናል” አለው።+
23 ዳዊትም ይሖዋን ጠየቀ፤ እሱ ግን እንዲህ አለው፦ “በቀጥታ አትውጣ። ይልቁንም ከኋላቸው ዞረህ በባካ* ቁጥቋጦዎቹ ፊት ለፊት ግጠማቸው። 24 በባካ ቁጥቋጦዎቹ አናት ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማ ቆራጥ እርምጃ ውሰድ፤ ምክንያቱም ይህ በሚሆንበት ጊዜ ይሖዋ የፍልስጤማውያንን ሠራዊት ለመምታት በፊትህ ወጥቷል ማለት ነው።”
15 የእውነተኛው አምላክ ሰው አገልጋይ በማለዳ ተነስቶ ወደ ውጭ ሲወጣ በፈረሶችና በጦር ሠረገሎች የተጠናከረ ሠራዊት ከተማዋን መክበቡን አየ። አገልጋዩም ወዲያውኑ “ወየው ጌታዬ! ምን ብናደርግ ይሻላል?” አለ። 16 ኤልሳዕ ግን “አይዞህ፣ አትፍራ!+ ከእነሱ ጋር ካሉት ከእኛ ጋር ያሉት ይበልጣሉ”+ አለው።