-
2 ሳሙኤል 17:27-29አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
27 ዳዊት ማሃናይም ሲደርስ የአሞናውያን ከተማ ከሆነችው ከራባ+ የመጣው የናሃሽ ልጅ ሾባይ፣ ከሎደባር የመጣው የአሚዔል ልጅ ማኪርና+ ከሮገሊም የመጣው ጊልያዳዊው ቤርዜሊ+ 28 ለመኝታ የሚሆኑ ነገሮች፣ ጎድጓዳ ሳህኖች፣ የሸክላ ዕቃዎች፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ዱቄት፣ ቆሎ፣ ባቄላ፣ ምስር፣ የተጠበሰ እሸት፣ 29 ማር፣ ቅቤ፣ በግና አይብ* ይዘው መጡ። ይህን ሁሉ ይዘው የመጡት “መቼም ሕዝቡ በምድረ በዳ ተርቧል፣ ደክሟል፣ ተጠምቷል” ብለው በማሰብ ዳዊትና አብረውት የነበሩት ሰዎች እንዲበሉት ነው።+
-