-
ኢያሱ 12:2, 3አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
2 በሃሽቦን የሚኖረውና በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ላይ በምትገኘው በአሮዔር+ ሆኖ የሚገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሲሖን፤+ እሱም በአርኖን ሸለቆ+ መሃል ካለው ስፍራ አንስቶ የአሞናውያን ወሰን እስከሆነው እስከ ያቦቅ ሸለቆ* ድረስ ያለውን የጊልያድን እኩሌታ ይገዛ ነበር። 3 በተጨማሪም ምሥራቃዊ አረባን እስከ ኪኔሬት ባሕር*+ ድረስ፣ በስተ ምሥራቅ በቤትየሺሞት አቅጣጫ እስካለው የአረባ ባሕር ይኸውም እስከ ጨው ባሕር* ድረስና በስተ ደቡብ እስከ ጲስጋ+ ሸንተረር ድረስ ያለውን አካባቢ ይገዛ ነበር።
-