-
1 ዜና መዋዕል 21:16, 17አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
16 ዳዊት ቀና ብሎ ሲመለከት የይሖዋ መልአክ በምድርና በሰማያት መካከል ቆሞ አየ፤ እሱም በኢየሩሳሌም ላይ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ነበር።+ ዳዊትና ሽማግሌዎቹ ማቅ+ እንደለበሱ ወዲያውኑ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፉ።+ 17 ዳዊትም እውነተኛውን አምላክ እንዲህ አለ፦ “ሕዝቡ እንዲቆጠር ያዘዝኩት እኔ አይደለሁም? ኃጢአት የሠራሁት እኔ ነኝ፤ በደል የፈጸምኩትም እኔ ነኝ፤+ ታዲያ እነዚህ በጎች ምን አደረጉ? አምላኬ ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፤ በሕዝብህ ላይ ግን ይህን መቅሰፍት አታውርድ።”+
-