46 ከዚያም ሙሴ አሮንን እንዲህ አለው፦ “የዕጣን ማጨሻ ውሰድና ከመሠዊያው ላይ እሳት አድርግበት፤+ በላዩም ላይ ዕጣን ጨምርበት፤ ፈጥነህም ወደ ማኅበረሰቡ በመሄድ አስተሰርይላቸው፤+ ምክንያቱም ይሖዋ ተቆጥቷል። መቅሰፍቱ ጀምሯል!” 47 አሮን ልክ ሙሴ እንዳለው ወዲያውኑ የዕጣን ማጨሻውን ይዞ ወደ ጉባኤው መካከል እየሮጠ ገባ፤ መቅሰፍቱ በሕዝቡ መካከል ጀምሮ ነበር። በመሆኑም ዕጣኑን በዕጣን ማጨሻው ላይ በማድረግ ለሕዝቡ ማስተሰረይ ጀመረ።