ዘኁልቁ 9:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 “‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት።+ ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት።+ ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’”+ ሩት 1:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+ 2 ነገሥት 5:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው። 2 ዜና መዋዕል 6:32, 33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 32 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣* ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣+ 33 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና+ እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት። ኢሳይያስ 56:6, 7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+ የሐዋርያት ሥራ 8:27 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ* ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም* አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤+
14 “‘በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ካለ እሱም ለይሖዋ የፋሲካን መሥዋዕት ማዘጋጀት አለበት።+ ይህን በፋሲካው ደንብና በወጣለት ሥርዓት መሠረት ማድረግ አለበት።+ ለሁላችሁም ማለትም ለባዕድ አገሩም ሰው ሆነ ለአገሬው ተወላጅ አንድ ዓይነት ደንብ ይኑር።’”+
16 ሩት ግን እንዲህ አለቻት፦ “ከአንቺ እንድለይና ትቼሽ እንድመለስ አትማጸኚኝ፤ እኔ እንደሆነ ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ፤ በምታድሪበት አድራለሁ። ሕዝብሽ ሕዝቤ፣ አምላክሽም አምላኬ ይሆናል።+
15 ከዚያ በኋላ አጃቢዎቹን አስከትሎ ወደ እውነተኛው አምላክ ሰው ተመለሰ፤+ በፊቱም ቆሞ “በእስራኤል እንጂ በምድር ላይ በሌላ በየትኛውም ቦታ አምላክ እንደሌለ አሁን አውቄአለሁ።+ እባክህ ከአገልጋይህ ስጦታ* ተቀበል” አለው።
32 “በተጨማሪም ከሕዝብህ ከእስራኤል ወገን ያልሆነ የባዕድ አገር ሰው ከታላቁ ስምህ፣* ከኃያሉ እጅህና ከተዘረጋው ክንድህ የተነሳ ከሩቅ አገር ቢመጣ፣+ ወደዚህም ቤት መጥቶ ቢጸልይ፣+ 33 ከመኖሪያ ቦታህ ከሰማያት ሆነህ ስማ፤ የምድር ሕዝቦች ሁሉ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ስምህን እንዲያውቁና+ እንዲፈሩህ እንዲሁም ስምህ እኔ በሠራሁት በዚህ ቤት እንደሚጠራ እንዲያውቁ ያ የባዕድ አገር ሰው የጠየቀህን ሁሉ ፈጽምለት።
6 እሱን ለማገልገል፣ የይሖዋን ስም ለመውደድናየእሱ አገልጋዮች ለመሆንከይሖዋ ጋር የሚቆራኙትን የባዕድ አገር ሰዎች፣+ሰንበትን የሚጠብቁትንና የማያረክሱትን፣ቃል ኪዳኔንም አጥብቀው የሚይዙትን ሁሉ፣ 7 ቅዱስ ወደሆነው ተራራዬ አመጣቸዋለሁ፤+በጸሎት ቤቴም ውስጥ እጅግ እንዲደሰቱ አደርጋቸዋለሁ። የሚያቀርቧቸውም ሙሉ በሙሉ የሚቃጠሉ መባዎችና መሥዋዕቶች በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት ያገኛሉ። ቤቴም ለሕዝቦች ሁሉ የጸሎት ቤት ተብሎ ይጠራልና።”+
27 እሱም ተነስቶ ሄደ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ* ባለሥልጣንና የገንዘቧ ሁሉ ኃላፊ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባም* አገኘ። ይህ ሰው ለአምልኮ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤+