-
1 ነገሥት 21:4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 በመሆኑም አክዓብ ኢይዝራኤላዊው ናቡቴ “የአባቶቼን ርስት አልሰጥህም” ስላለው ፊቱ ጠቁሮና አዝኖ ወደ ቤቱ ገባ። ከዚያም ፊቱን ወደ ግድግዳ አዙሮ ተኛ፤ ምግብ ለመብላትም ፈቃደኛ አልሆነም።
-
-
1 ነገሥት 21:20-22አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
20 አክዓብም ኤልያስን “ጠላቴ ሆይ፣ አገኘኸኝ?” አለው፤+ እሱም እንዲህ አለው፦ “አዎ፣ አግኝቼሃለሁ። ‘እንግዲህ አንተ በይሖዋ ፊት መጥፎ የሆነውን ነገር ለማድረግ ቆርጠህ ስለተነሳህ*+ 21 ጥፋት አመጣብሃለሁ፤ እየተከታተልኩም ሙልጭ አድርጌ እጠርግሃለሁ፤ እንዲሁም በእስራኤል ውስጥ የሚገኘውን ምስኪኑንና ደካማውን+ ጨምሮ የአክዓብ የሆነውን ወንድ* ሁሉ አጠፋለሁ።+ 22 ቁጣዬን ስላነሳሳህና እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲፈጽሙ ስላደረግክ ቤትህን እንደ ናባጥ ልጅ እንደ ኢዮርብዓም+ ቤትና እንደ አኪያህ ልጅ እንደ ባኦስ+ ቤት አደርገዋለሁ።’
-