-
1 ነገሥት 9:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ከዚያም እንዲህ ይላሉ፦ ‘ይህ የደረሰባቸው አባቶቻቸውን ከግብፅ ምድር ያወጣውን አምላካቸውን ይሖዋን ትተው ሌሎች አማልክትን ስለተከተሉና ለእነሱ ስለሰገዱ እንዲሁም እነሱን ስላገለገሉ ነው። ይሖዋ ይህን ሁሉ መከራ ያመጣባቸው ለዚህ ነው።’”+
-
-
1 ነገሥት 16:30-33አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
30 የኦምሪ ልጅ አክዓብ ከእሱ በፊት የነበሩት ሁሉ ከፈጸሙት የከፋ ድርጊት በይሖዋ ፊት ፈጸመ።+ 31 አክዓብ የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም+ በተከተለው የኃጢአት ጎዳና መመላለሱ ሳያንሰው የሲዶናውያን+ ንጉሥ የኤትባዓል ልጅ የሆነችውን ኤልዛቤልን+ አገባ፤ እንዲሁም ባአልን ማገልገልና+ ለእሱ መስገድ ጀመረ። 32 እንዲሁም በሰማርያ ለባአል በሠራው ቤት+ ውስጥ* ለባአል መሠዊያ አቆመ። 33 በተጨማሪም አክዓብ የማምለኪያ ግንድ* ሠራ።+ እንዲሁም ከእሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ይበልጥ የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን የሚያስቆጣ ድርጊት ፈጸመ።
-