19 ቆም ብሎ በልቡ ያሰበ
ወይም እውቀትም ሆነ ማስተዋል ኖሮት እንዲህ ብሎ የተናገረ የለም፦
“ግማሹን እሳት አንድጄበታለሁ፤
በፍሙም ላይ ዳቦ ጋግሬአለሁ፤ ሥጋም ጠብሼ በልቻለሁ።
ታዲያ በቀረው እንጨት አስጸያፊ ነገር መሥራቴ ተገቢ ነው?+
ከዛፍ ለተቆረጠ እንጨት መስገድ ይገባኛል?”
20 እሱ አመድ ይበላል።
የተታለለው የገዛ ልቡ አስቶታል።
ራሱን ሊያድን አይችልም፤
ደግሞም “በቀኝ እጄ ያለው ውሸት አይደለም?” አይልም።