23 በኋላም ወደ ማራ+ መጡ፤ ያም ሆኖ በማራ ያለው ውኃ መራራ ስለነበር ሊጠጡት አልቻሉም። የቦታውን ስም ማራ ያለውም በዚህ የተነሳ ነው። 24 በመሆኑም ሕዝቡ “እንግዲህ ምን ልንጠጣ ነው?” እያለ በሙሴ ላይ ማጉረምረም ጀመረ።+ 25 እሱም ወደ ይሖዋ ጮኸ፤+ ይሖዋም ወደ አንዲት ዛፍ መራው። ሙሴም ዛፏን ውኃው ውስጥ ሲጥላት ውኃው ጣፋጭ ሆነ።
እሱም በዚያ የሚመሩበት ሥርዓትና ለፍርድ መሠረት የሚሆን መመሪያ አወጣላቸው፤ በዚያም ፈተናቸው።+