ማቴዎስ 10:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የታመሙትን ፈውሱ፤+ የሞቱትን አስነሱ፤ የሥጋ ደዌ ያለባቸውን አንጹ፤ አጋንንትንም አስወጡ። በነፃ እንደተቀበላችሁ በነፃ ስጡ። ሉቃስ 12:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያም “አንድ ሰው ሀብታም ቢሆንም እንኳ ንብረቱ ሕይወት ሊያስገኝለት አይችልም፤+ ስለዚህ ተጠንቀቁ፤ ከስግብግብነትም* ሁሉ ተጠበቁ”+ አላቸው። የሐዋርያት ሥራ 20:33 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 33 የማንንም ብር፣ ወርቅ ወይም ልብስ አልተመኘሁም።+ 1 ጢሞቴዎስ 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።+
10 የገንዘብ ፍቅር የብዙ ዓይነት ጎጂ ነገሮች ሥር ነውና፤ አንዳንዶች በዚህ ፍቅር ተሸንፈው ከእምነት ጎዳና ስተው ወጥተዋል፤ እንዲሁም ሁለንተናቸውን በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።+