5 ስለዚህ አምላኩ ይሖዋ በሶርያ ንጉሥ+ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እነሱም ድል አደረጉት፤ ከሕዝቡም መካከል ብዙዎቹን ማርከው ወደ ደማስቆ+ ወሰዱ። ደግሞም አምላክ በእስራኤል ንጉሥ እጅ አሳልፎ ሰጠው፤ እሱም ከባድ እልቂት አደረሰበት። 6 የረማልያህ ልጅ ፋቁሄ+ በይሁዳ 120,000 ሰዎችን በአንድ ቀን የገደለ ሲሆን ሁሉም ደፋር ተዋጊዎች ነበሩ፤ ይህም የሆነው የአባቶቻቸውን አምላክ ይሖዋን በመተዋቸው ነው።+