ዘዳግም 7:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+ ዘዳግም 12:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+ 2 ዜና መዋዕል 31:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።
5 “ከዚህ ይልቅ እንዲህ አድርጉባቸው፦ መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን ሰባብሩ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውን* ቆራርጡ፤+ የተቀረጹ ምስሎቻቸውንም በእሳት አቃጥሉ።+
3 መሠዊያዎቻቸውን አፈራርሱ፤ የማምለኪያ ዓምዶቻቸውን አድቅቁ፤+ የማምለኪያ ግንዶቻቸውንም* በእሳት አቃጥሉ፤ የአማልክታቸውን የተቀረጹ ምስሎች ሰባብራችሁ ጣሉ፤+ ስማቸውንም ከዚያ ስፍራ ሙሉ በሙሉ ደምስሱ።+
31 ከዚህ በኋላ በዚያ የተገኙት እስራኤላውያን በሙሉ ወደ ይሁዳ ከተሞች ወጥተው በመላው ይሁዳና ቢንያም እንዲሁም በኤፍሬምና በምናሴ+ የነበሩትን የማምለኪያ ዓምዶች+ ሰባበሩ፤ የማምለኪያ ግንዶቹን*+ ቆረጡ፤ ከፍ ያሉትንም የማምለኪያ ቦታዎችና+ መሠዊያዎቹን+ አፈራረሱ፤ ምንም ያስቀሩት ነገር አልነበረም፤ ከዚህ በኋላ እስራኤላውያን በሙሉ ወደየከተሞቻቸው፣ እያንዳንዳቸውም ወደየርስታቸው ተመለሱ።