-
ዘፍጥረት 36:31-39አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
31 እነዚህ በእስራኤላውያን* ላይ የትኛውም ንጉሥ መግዛት ከመጀመሩ በፊት+ በኤዶም ምድር ይገዙ የነበሩ ነገሥታት ናቸው።+ 32 የቢዖር ልጅ ቤላ በኤዶም ይገዛ ነበር፤ የከተማውም ስም ዲንሃባ ይባል ነበር። 33 ቤላ ሲሞት የቦስራው የዛራ ልጅ ዮባብ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 34 ዮባብ ሲሞት ከቴማናውያን ምድር የመጣው ሁሻም በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 35 ሁሻም ሲሞት ምድያማውያንን+ በሞዓብ ክልል* ድል ያደረጋቸው የቤዳድ ልጅ ሃዳድ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ፤ የከተማውም ስም አዊት ይባል ነበር። 36 ሃዳድ ሲሞት የማስረቃው ሳምላ በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 37 ሳምላ ሲሞት በወንዙ አጠገብ ያለው የረሆቦቱ ሻኡል በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 38 ሻኡል ሲሞት የአክቦር ልጅ ባአልሀናን በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። 39 የአክቦር ልጅ ባአልሀናን ሲሞት ሃዳር በእሱ ምትክ መግዛት ጀመረ። የከተማው ስም ጳኡ ነበር፤ የሚስቱም ስም መሄጣቤል ሲሆን እሷም የመዛሃብ ሴት ልጅ የማጥሬድ ልጅ ናት።
-