30 ከዚያም የማልካምን ዘውድ ከራሱ ላይ ወሰደ። የዘውዱም ክብደት አንድ ታላንት ወርቅ ነበር፤ በላዩም ላይ የከበሩ ድንጋዮች ነበሩ፤ ዘውዱም በዳዊት ራስ ላይ ተደረገ። በተጨማሪም ከከተማዋ+ በጣም ብዙ ምርኮ ወሰደ።+ 31 ነዋሪዎቿንም አውጥቶ ድንጋይ እንዲቆርጡ፣ ስለት ባላቸው የብረት መሣሪያዎችና በብረት መጥረቢያዎች እንዲሠሩ እንዲሁም ጡብ እንዲያመርቱ አደረጋቸው። በአሞናውያን ከተሞች ሁሉ እንዲሁ አደረገ። በመጨረሻም ዳዊትና ሠራዊቱ ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።