ዘሌዋውያን 9:23, 24 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 በመጨረሻም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ገቡ፤ ከዚያም ወጥተው ሕዝቡን ባረኩ።+ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤+ 24 እሳትም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ+ በመሠዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠል መባና ስብ በላ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያይ እልል አለ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።+ 1 ነገሥት 18:38 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 38 በዚህ ጊዜ የይሖዋ እሳት ወርዶ የሚቃጠለውን መባ፣ እንጨቱን፣ ድንጋዮቹንና አፈሩን በላ፤+ በቦዩ ውስጥ የነበረውንም ውኃ ላሰ።+ 2 ዜና መዋዕል 7:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ሰለሞንም ጸሎቱን እንደጨረሰ+ እሳት ከሰማያት ወርዶ+ የሚቃጠለውን መባና መሥዋዕቶቹን በላ፤ የይሖዋም ክብር ቤቱን ሞላው።+
23 በመጨረሻም ሙሴና አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ገቡ፤ ከዚያም ወጥተው ሕዝቡን ባረኩ።+ በዚህ ጊዜ የይሖዋ ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ፤+ 24 እሳትም ከይሖዋ ፊት ወጥቶ+ በመሠዊያው ላይ ያለውን የሚቃጠል መባና ስብ በላ። ሕዝቡም ሁሉ ይህን ሲያይ እልል አለ፤ በግንባሩም መሬት ላይ ተደፋ።+