10 ደህንነቱን እንዲጠይቅና ከሃዳድኤዜር ጋር ተዋግቶ ድል በማድረጉ የተሰማውን ደስታ እንዲገልጽለት ልጁን ሃዶራምን ወዲያውኑ ወደ ንጉሥ ዳዊት ላከው (ሃዳድኤዜር ከቶዑ ጋር ብዙ ጊዜ ይዋጋ ነበርና)፤ እሱም ከወርቅ፣ ከብርና ከመዳብ የተሠሩ ብዙ ዓይነት ዕቃዎችን ይዞ መጣ። 11 ንጉሥ ዳዊት እነዚህን ዕቃዎች ከሁሉም ብሔራት ይኸውም ከኤዶም፣ ከሞዓብ፣ ከአሞናውያን፣+ ከፍልስጤማውያንና+ ከአማሌቃውያን+ ከማረከው ብርና ወርቅ ጋር ለይሖዋ ቀደሰ።+