-
ኤርምያስ 32:42አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
42 “ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ ‘በዚህ ሕዝብ ላይ ይህን ሁሉ ታላቅ ጥፋት እንዳመጣሁ፣ ልክ እንዲሁ ቃል የገባሁላቸውን መልካም ነገር ሁሉ አመጣላቸዋለሁ።+
-
-
ኤርምያስ 33:10, 11አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
10 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ 11 አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣+ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!”+ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’
“‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይዘው ይመጣሉ’+ ይላል ይሖዋ።”
-