-
1 ነገሥት 8:64-66አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
64 ንጉሡም በዚያ ቀን በይሖዋ ቤት ፊት የሚገኘውን የግቢውን መሃል መቀደስ አስፈልጎት ነበር፤ ምክንያቱም የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን በዚያ ማቅረብ ነበረበት፤ ይህም የሆነው በይሖዋ ፊት ያለው የመዳብ መሠዊያ+ የሚቃጠሉትን መሥዋዕቶች፣ የእህል መባዎቹንና የኅብረት መሥዋዕቶቹን ስብ+ መያዝ ስላልቻለ ነው። 65 በዚያ ጊዜ ሰለሞን ከመላው እስራኤል ጋር ይኸውም ከሌቦሃማት* አንስቶ እስከ ግብፅ ደረቅ ወንዝ*+ ድረስ ካለው ምድር ከመጣው ታላቅ ጉባኤ ጋር በመሆን በአምላካችን በይሖዋ ፊት ለ7 ቀን፣ ከዚያም ለተጨማሪ 7 ቀን በአጠቃላይ ለ14 ቀን በዓሉን አከበረ።+ 66 በቀጣዩም* ቀን ሕዝቡን አሰናበተ፤ እነሱም ንጉሡን ባረኩ፤ ይሖዋ ለአገልጋዩ ለዳዊትና ለሕዝቡ ለእስራኤል ባሳየው ጥሩነት ሁሉ እየተደሰቱና ከልባቸው እየፈነደቁ+ ወደየቤታቸው ሄዱ።
-