11 ከዚያም አምላክ ሰለሞንን እንዲህ አለው፦ “የልብህ መሻት ይህ ስለሆነ ደግሞም ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር ወይም የሚጠሉህን ሰዎች ሞት አሊያም ረጅም ዕድሜ ስላልተመኘህ፣ ይልቁንም አንተን ንጉሥ አድርጌ የሾምኩበትን ሕዝቤን ማስተዳደር እንድትችል ጥበብና እውቀት ስለጠየቅክ፣+ 12 ጥበብና እውቀት ይሰጥሃል፤ ከዚህም ሌላ ከአንተ በፊት የነበረ ማንኛውም ንጉሥ ያላገኘውን፣ ከአንተም በኋላ የሚነሳ የትኛውም ንጉሥ የማያገኘውን ብልጽግና፣ ሀብትና ክብር እሰጥሃለሁ።”+