1 ነገሥት 15:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች ግን አልተወገዱም ነበር።+ ያም ሆኖ አሳ በሕይወት ዘመኑ* ሁሉ ልቡ በይሖዋ ዘንድ ሙሉ* ነበር። 1 ነገሥት 22:43 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 43 እሱም በአባቱ በአሳ+ መንገድ ሁሉ ሄደ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም፤ በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤ ሕዝቡም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ መሠዋቱንና የሚጨስ መሥዋዕት ማቅረቡን አልተወም ነበር።+ 2 ዜና መዋዕል 17:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ልጁ ኢዮሳፍጥም+ በምትኩ ነገሠ፤ በእስራኤልም ላይ ሥልጣኑን አጠናከረ። 2 ዜና መዋዕል 17:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ልቡም የይሖዋን መንገዶች በድፍረት ተከተለ፤ ደግሞም ከፍ ያሉትን የማምለኪያ ቦታዎችና የማምለኪያ ግንዶቹን* ከይሁዳ አስወገደ።+
43 እሱም በአባቱ በአሳ+ መንገድ ሁሉ ሄደ። ከዚያ ፈቀቅ አላለም፤ በይሖዋም ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አደረገ።+ ይሁን እንጂ ከፍ ያሉት የማምለኪያ ቦታዎች አልተወገዱም ነበር፤ ሕዝቡም ከፍ ባሉት የማምለኪያ ቦታዎች ላይ መሠዋቱንና የሚጨስ መሥዋዕት ማቅረቡን አልተወም ነበር።+