መሳፍንት 2:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ይሖዋ መሳፍንትን በሚያስነሳላቸው+ ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ከመስፍኑ ጋር ይሆን ነበር፤ በመስፍኑም ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በሚጨቁኗቸውና+ በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ ያዝናል።*+ መሳፍንት 3:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+ መሳፍንት 3:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ከዚያም እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ ጮኹ፤+ ይሖዋም ግራኝ+ የሆነውን ቢንያማዊውን+ የጌራን ልጅ ኤሁድን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው።+ ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በእሱ በኩል ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን ግብር ላኩ። 1 ሳሙኤል 12:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚያም ይሖዋ ያለስጋት መኖር እንድትችሉ የሩባአልን፣+ ቤዳንን፣ ዮፍታሔንና+ ሳሙኤልን+ ልኮ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ እጅ ታደጋችሁ።+ 2 ነገሥት 13:4, 5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ከጊዜ በኋላ ኢዮዓካዝ የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ለመነ፤ ይሖዋም ሰማው፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጭቆና አይቶ ነበር።+ 5 ስለሆነም ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከሶርያውያን እጅ ነፃ የሚያወጣ አዳኝ ሰጣቸው፤+ እስራኤላውያንም እንደቀድሟቸው በየቤታቸው መኖር ጀመሩ።*
18 ይሖዋ መሳፍንትን በሚያስነሳላቸው+ ጊዜ ሁሉ ይሖዋ ከመስፍኑ ጋር ይሆን ነበር፤ በመስፍኑም ዘመን ሁሉ ከጠላቶቻቸው እጅ ያድናቸው ነበር፤ ምክንያቱም ይሖዋ በሚጨቁኗቸውና+ በሚያንገላቷቸው ሰዎች የተነሳ ሲቃትቱ ያዝናል።*+
9 ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ በጮኹም ጊዜ+ ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዲያድናቸው የካሌብ ታናሽ ወንድም የሆነውን የቀናዝን ልጅ ኦትኒኤልን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳው።+
15 ከዚያም እስራኤላውያን ይሖዋ እንዲረዳቸው ወደ እሱ ጮኹ፤+ ይሖዋም ግራኝ+ የሆነውን ቢንያማዊውን+ የጌራን ልጅ ኤሁድን+ አዳኝ አድርጎ አስነሳላቸው።+ ከጊዜ በኋላ እስራኤላውያን በእሱ በኩል ለሞዓብ ንጉሥ ለኤግሎን ግብር ላኩ።
4 ከጊዜ በኋላ ኢዮዓካዝ የይሖዋን ሞገስ ለማግኘት ለመነ፤ ይሖዋም ሰማው፤ ምክንያቱም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ ያደረሰውን ጭቆና አይቶ ነበር።+ 5 ስለሆነም ይሖዋ ለእስራኤላውያን ከሶርያውያን እጅ ነፃ የሚያወጣ አዳኝ ሰጣቸው፤+ እስራኤላውያንም እንደቀድሟቸው በየቤታቸው መኖር ጀመሩ።*