2 በመሆኑም ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር+ የመጀመሪያ ቀን ላይ ወንዶችን፣ ሴቶችንና የሚነገረውን ነገር ሰምተው ማስተዋል የሚችሉትን ሁሉ ወዳቀፈው ጉባኤ ሕጉን አመጣ።+ 3 እሱም ከውኃ በር ፊት ለፊት በሚገኘው አደባባይ በተሰበሰቡት ወንዶች፣ ሴቶችና ሰምተው ማስተዋል በሚችሉ ሁሉ ፊት ድምፁን ከፍ አድርጎ ከማለዳ እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሕጉን አነበበ፤+ ሕዝቡም የሕጉ መጽሐፍ ሲነበብ በትኩረት አዳመጡ።+