ዘፀአት 12:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 እኩለ ሌሊት ላይ ይሖዋ፣ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ በእስር ቤት* እስከሚገኘው እስረኛ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ መታ፤ የእያንዳንዱን እንስሳ በኩርም መታ።+ መዝሙር 73:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ክፉ ሰዎች ያላቸውን ሰላም በተመለከትኩ ጊዜ፣እብሪተኛ በሆኑ ሰዎች* ቀንቼ ነበርና።+ መዝሙር 73:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እንዴት በቅጽበት ጠፉ!+ በአስደንጋጭ ሁኔታ ተደመሰሱ! የደረሰባቸው ጥፋት ቅጽበታዊ ነው! ዳንኤል 5:30 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 30 በዚያኑ ሌሊት ከለዳዊው ንጉሥ ቤልሻዛር ተገደለ።+ የሐዋርያት ሥራ 12:21-23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 21 አንድ ልዩ ዝግጅት በተደረገበት ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ለሕዝቡ ንግግር መስጠት ጀመረ። 22 የተሰበሰበውም ሕዝብ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው አይደለም!” እያለ ይጮኽ ጀመር። 23 በዚህ ጊዜ፣ ለአምላክ ክብር ባለመስጠቱ ወዲያውኑ የይሖዋ* መልአክ ቀሰፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።
29 እኩለ ሌሊት ላይ ይሖዋ፣ በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠው ከፈርዖን የበኩር ልጅ አንስቶ በእስር ቤት* እስከሚገኘው እስረኛ የበኩር ልጅ ድረስ በግብፅ ምድር ያለውን በኩር ሁሉ መታ፤ የእያንዳንዱን እንስሳ በኩርም መታ።+
21 አንድ ልዩ ዝግጅት በተደረገበት ቀን ሄሮድስ ልብሰ መንግሥቱን ለብሶ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፤ ከዚያም ለሕዝቡ ንግግር መስጠት ጀመረ። 22 የተሰበሰበውም ሕዝብ “ይህ የአምላክ ድምፅ ነው እንጂ የሰው አይደለም!” እያለ ይጮኽ ጀመር። 23 በዚህ ጊዜ፣ ለአምላክ ክብር ባለመስጠቱ ወዲያውኑ የይሖዋ* መልአክ ቀሰፈው፤ በትል ተበልቶም ሞተ።