መዝሙር 44:23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 23 ይሖዋ ሆይ፣ ተነስ። ለምንስ ትተኛለህ?+ ንቃ! ለዘላለም አትጣለን።+ ኢሳይያስ 42:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ይሖዋ እንደ ኃያል ሰው ይወጣል።+ እንደ ተዋጊ ቅንዓቱን ይቀሰቅሳል።+ ይጮኻል፤ አዎ፣ ቀረርቶ ያሰማል፤ከጠላቶቹ ይበልጥ ኃያል መሆኑን ያሳያል።+