1 ዜና መዋዕል 21:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ስለዚህ ዳዊት ጋድን እንዲህ አለው፦ “ሁኔታው በጣም አስጨንቆኛል። ምሕረቱ እጅግ ታላቅ ስለሆነ+ እባክህ በይሖዋ እጅ ልውደቅ፤ ሰው እጅ ላይ ግን አትጣለኝ።”+ መዝሙር 86:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ግን መሐሪና ሩኅሩኅ፣*ለቁጣ የዘገየህ እንዲሁም ታማኝ ፍቅርህና ታማኝነትህ* የበዛ አምላክ ነህ።+ ኢሳይያስ 55:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ክፉ ሰው መንገዱን፣መጥፎ ሰውም ሐሳቡን ይተው፤+ምሕረት ወደሚያሳየው አምላካችን ወደ ይሖዋ ይመለስ፤+ይቅርታው ብዙ ነውና።*+ 2 ቆሮንቶስ 1:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 የምሕረት* አባትና+ የመጽናናት+ ሁሉ አምላክ የሆነው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት+ ይወደስ፤ ያዕቆብ 5:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች* እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን።+ ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤+ በውጤቱም ይሖዋ* ያደረገለትን አይታችኋል፤+ በዚህም ይሖዋ* እጅግ አፍቃሪና* መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።+
13 ስለዚህ ዳዊት ጋድን እንዲህ አለው፦ “ሁኔታው በጣም አስጨንቆኛል። ምሕረቱ እጅግ ታላቅ ስለሆነ+ እባክህ በይሖዋ እጅ ልውደቅ፤ ሰው እጅ ላይ ግን አትጣለኝ።”+
11 እነሆ፣ የጸኑትን ደስተኞች* እንደሆኑ አድርገን እንቆጥራቸዋለን።+ ስለ ኢዮብ ጽናት ሰምታችኋል፤+ በውጤቱም ይሖዋ* ያደረገለትን አይታችኋል፤+ በዚህም ይሖዋ* እጅግ አፍቃሪና* መሐሪ እንደሆነ ተመልክታችኋል።+