2 ነገሥት 6:17 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+ መዝሙር 91:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 በመንገድህ ሁሉ እንዲጠብቁህ+መላእክቱን ስለ አንተ ያዛልና።+ ማቴዎስ 18:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 በሰማይ ያሉት መልአኮቻቸው በሰማይ ባለው አባቴ ፊት ዘወትር ስለሚቀርቡ ከእነዚህ ከትናንሾቹ መካከል አንዱንም እንዳትንቁ ተጠንቀቁ።+ ዕብራውያን 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 በተጨማሪም ስለ መላእክት ሲናገር “መላእክቱን መናፍስት፣ አገልጋዮቹን*+ ደግሞ የእሳት ነበልባል ያደርጋል”+ ይላል። ዕብራውያን 1:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ሁሉም መዳን የሚወርሱትን እንዲያገለግሉ የሚላኩ ቅዱስ አገልግሎት* የሚያከናውኑ መናፍስት አይደሉም?+
17 ከዚያም ኤልሳዕ “ይሖዋ ሆይ፣ እባክህ ያይ ዘንድ ዓይኖቹን ክፈትለት”+ በማለት ጸለየ። ይሖዋም ወዲያውኑ የአገልጋዩን ዓይኖች ከፈተ፤ እሱም አየ፤ እነሆ የእሳት ፈረሶችና የጦር ሠረገሎች+ በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራማውን አካባቢ ሞልተውት ነበር።+