ዘፀአት 19:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 የሲና ተራራ ይሖዋ በእሳት ስለወረደበት ዙሪያውን ጨሰ፤+ ጭሱም እንደ እቶን ጭስ እየተትጎለጎለ ይወጣ ነበር፤ ተራራውም ሁሉ በኃይል ተናወጠ።+ ዳንኤል 7:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 “እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ዙፋኖች ተዘጋጁ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውም+ ተቀመጠ።+ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ፣+ የራሱም ፀጉር እንደጠራ ሱፍ ነበር። ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኮራኩሮቹም የሚነድ እሳት ነበሩ።+ 10 ከፊቱ የእሳት ጅረት ይፈልቅና ይፈስ ነበር።+ ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍም* በፊቱ ቆመው ነበር።+ ችሎቱ+ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ። ዕብራውያን 12:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 አምላካችን የሚባላ እሳት ነውና።+
9 “እኔም እየተመለከትኩ ሳለ ዙፋኖች ተዘጋጁ፤ ከዘመናት በፊት የነበረውም+ ተቀመጠ።+ ልብሱ እንደ በረዶ ነጭ፣+ የራሱም ፀጉር እንደጠራ ሱፍ ነበር። ዙፋኑ የእሳት ነበልባል፣ መንኮራኩሮቹም የሚነድ እሳት ነበሩ።+ 10 ከፊቱ የእሳት ጅረት ይፈልቅና ይፈስ ነበር።+ ሺህ ጊዜ ሺዎች ያገለግሉት ነበር፤ እልፍ ጊዜ እልፍም* በፊቱ ቆመው ነበር።+ ችሎቱ+ ተሰየመ፤ መጻሕፍትም ተከፈቱ።