ማቴዎስ 15:18 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 18 ይሁን እንጂ ከአፍ የሚወጣ ሁሉ ከልብ ይወጣል፤ ሰውንም የሚያረክሰው ይህ ነው።+ ኤፌሶን 4:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎችን የሚያንጽና ሰሚዎቹን ሊጠቅም የሚችል መልካም ቃል ብቻ+ እንጂ የበሰበሰ ቃል ከቶ ከአፋችሁ አይውጣ።+ ያዕቆብ 3:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ምላስም እሳት ናት።+ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የክፋትን ዓለም ትወክላለች፤ መላ ሰውነትን ታረክሳለችና፤+ እንዲሁም መላውን የሕይወት ጎዳና* ታቃጥላለች፤ እሷም በገሃነም* ትቃጠላለች። ያዕቆብ 3:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 በምላሳችን አባት የሆነውን ይሖዋን* እናወድሳለን፤ ይሁንና በዚህችው ምላሳችን “በአምላክ አምሳል” የተፈጠሩትን ሰዎች+ እንረግማለን።
6 ምላስም እሳት ናት።+ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የክፋትን ዓለም ትወክላለች፤ መላ ሰውነትን ታረክሳለችና፤+ እንዲሁም መላውን የሕይወት ጎዳና* ታቃጥላለች፤ እሷም በገሃነም* ትቃጠላለች።